Amharic rendering of Overview of India’s Development Partnership

የህንድ ልማት አጋርነት አጭር መግለጫ  

 1. የህንድ መንግስት ስለ ልማት አጋርነት ያለው አመለካከት ህንድ ለነፃነት እና ወንድማማችነት ከሌሎች ቅኝ ተገዢ እና በማደግ ላይ ከሚገኙ ሀገራት ጋር ባለው የህንድ ትግል እና በማህተመ ጋንዲ አመራርነት “ማሰብ የምፈልገው ስለ መላው አለም ነው፡፡ አርብኝነቴ ለጠቅላላው የሰው ልጅ ጥሩ ማድረግን ይጨምራል፡፡ ስለሆነም የእኔ ለህንድአገልግሎት  የሰው ዘር አገልግሎትን ያካትታል፡፡” የተቃኘ ነው፡፡ ምንም እንኳን የሀብት ውሱንነት ያለባት ቢሆንም ህንድ የልማት ልምዷን እና የቴክኒክ ልምዷን ከሌሎች ሀገራት ጋር አለም አንድ ቤተሰብ ናት በሚል መንፈስ ታጋራለች፡፡
 2. የህንድ የልማት አመለካከት በዋናነት በሰው ላይ ማዕከል ያደረገ እና በማክበር፣ ብዝሃነት፣ ለወደፊቱ ክብካቤ በማድረግ፣ እና ዘላቂ ልማት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ለህንድ የትብብር ጠቃሚ መርህ የልማት አጋሮችን ማክበር እና በእነሱ የልማት ተቀዳሚ ትኩረት መመራት ነው፡፡ የህንድ የልማት ትብብር በሌላ በማንኛው ሁኔታ አልመጣም፡፡ የተከበሩ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር በሐምሌ 2018 እ.ኤ.አ በዩጋንዳ ፓርላማ ተገኝተው እንደተናገሩት “የእኛ የልማት አጋርነት ቅድሚያ በምንሰጣቸው ጉዳዮች ይመራል፡፡ለእናንተ በሚመች መልኩ የእናንተ እምቅ ችሎታ የሚያወጣ ሲሆን የወደፊታችሁንም አይገድብም… በተቻለ መጠን የሀገር ውስጥ አቅምን በመፍጠር በርካታ የሀገር ውስጥ እድሎችን እንፈጥራለን፡፡”
 3. የህንድ የልማት ትብብር የተቀናጀ ሲሆን በርካታ መሳሪያዎችን ለምሳሌ እርዳታ መስጠት፣ ብድር መስጠት፣ የአቅም ግንባታ እና የቴክኒክ ድጋፍን ያካትታል፡፡ ለአጋር አገራት በምንሰጠው ቅድሚያ ላይ ተመስርቶ የህንድ የልማት ትብብር ከንግድ እስከ ባህል፣ ከሐይል እስከ ምህንድስና፣ ከጤና እስከ ቤቶች ግንባታ፣ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እስከ መሰረተ ልማት፣ ከስፖርት እስከ ሳይንስ፣ ከአደጋ መከላከል እስከ ሰብአዊ ድጋፍ፣ ባህልን እና የቅርስ ሀብትን መጠበቅ እና መልሶ መተካትን ይጨምራል፡፡

የብድር አገልግሎት

 1. የልማት ድጋፍ በብድር አገልግሎት መልክ በህንድ መንግስት በህንድ ኢግዚም ባንክ አማካይነት ለህንድ ልማት እና የኢኮኖሚ ድጋፍ እቅድ ይቀርባል፡፡ ከ300 በላይ የብድር አገልግሎት  ለ64 ሀገራት 30.66 ቢሊየን ዩኤስ ዶላር ተሰጥቷል፡፡ በብድር አገልግሎት ስር ያሉ ፕሮጀክቶች ወሳኝ የመሰረተ ልማት ዘርፍ ለምሳሌ የትራንስፖርት ግንኙነት በባቡር፣ መንገድ እና ወደቦች የሀይል ማመንጨት እና ስርጭት፣ እርሻ እና መስኖ፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች፣ የጤና ጥበቃ፣ ትምህርት እና የአቅም ግንባታን ይጨምራል፡፡ በአንፃሩ ከ300 ብር በላይ የብድር አገልግሎት ፕሮጀክቶች የተጠናቀቁ ሲሆን ከ260 በላይ ፕሮጀክቶች በአተገባበር ላይ ይገኛሉ፡
 2. ከጠቅላላ 30.66 ቢሊየን ዩኤስ ዶላር የብድር አገልግሎት ውስጥ 15.90 ቢሊየን ዩኤስ ዶላር ለእስያ ሀገራት ለህንድ የቅርብ ጎረቤቶቿ ለሆኑ እና ትልቅ ቁርጠኝነት ላላቸው ሀገራት ተሰጥቷል፡፡ ለባንግላዲሽ 7.862 ቢሊየን ዩኤስ ዶላር፣ ለስሪላንካ 2.02 ቢሊየን ዩኤስ ዶላር፣ ለኔፓል 1.65 ቢሊየን ዩኤስ ዶላር፣ ለሞሪሺየስ 964.80 ሚሊየን ዩኤስ ዶላር፣ ለማልዳይቭስ 840 ሚሊየን ዩኤስ ዶላር፣ ለማይናማር 538.90 ሚሊየን ዩኤስ ዶላር እንዲሁም ለሲሸልስ 128 ሚሊየን ዩኤስ ዶላር ብድር ተሰጥቷል፡፡
 3. ህንድ በርካታ ምሳሌያዊ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ከአጋር አገራት ጋር በብድር አገልግሎት አጠናቃለች፡፡ አንድ አንድ ምሳሌያዊ ፕሮጀክቶች የጋምቢያ የፓርላማ ህንፃ፣ የጋና የፕሬዝዳንቱ ቤተመንግስት፣ የሀገሪቱን 1/3 የሀይል አገልግሎት የሚያቀርብ የሱዳን የኮስቲ ፓወር ፕሮጀክት፣ ለሀገሪቱ የሀይል አገልግሎት 1/4ኛ ሀይል የሚያቀርበው የሩዋንዳ ንያቦሮንጎ የሀይል ፕሮጀክት፣ የባንግላዲሽ የባቡር ድልድይ እና ሲግናል ሲስተም፣ የሴሪላንካ የድህረ ጦርነት የባቡር መልሶ ግንባታ ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡ ህንድ በብድር አገልግሎት እቅድ የመጀመሪያውን የሞንጎሊያ የነዳጅ ማጣሪያ በ1.24 ቢሊየን ዩኤስዲ ወጪ በመገንባት ላይ ስትሆን የባህር በር ለሌላት ሀገር ወሳኝ የሀይል ዋስትና ያቀርባል፡፡ ህንድ በበርካታ ሀገራት የመጀመሪያውን የኢንዱስትሪ ክፍል ለምሳሌ በጅቡቲ የመጀመሪያውን የሲሚንቶ ፋብሪካ፣ በሞሪታኒያ የመጀመሪያውን የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣ በጋና በመጀመሪያውን የስኳር ፋብሪካ ወዘተ ገንብታለች፡፡ በታንዛኒያ የላይኛው ሩቩ የውሃ ማከሚያ ተቋም በዳሬሰላም አከባቢ ለሚኖሩ ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃ ያቀርባል፡፡ የህንድ የብድር አገልግሎት በበርካታ አዳዲስ ዘርፎች ለምሳሌ መከላከያ እና የሶላር ኢነርጂ ተሰጥቷል፡፡
 4. እየተደረገ ያለው የህንድ መንግስት ድጋፍ በኢትዮጵያ የልማት ፕሮጀክቶች በብድር አገልግሎት ለኢትዮጵያ መንግስት ከ1 ቢሊየን ዩኤስ ዶላር በላይ በሆነ ገንዘብ የገጠር ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የስኳር ኢንዱስትሪ እና ባቡር አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡ ኢትዮጵያ ህንድ ለአፍሪካ ከምትሰጠው የረጅም ጊዜ ብድር ትልቋ ተጠቃሚ ሀገር ናት፡፡ የፊንጫ እና ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች እና ምዕራፍ 1 የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ በህንድ ኤግዚም ባንክ የብድር አገልግሎት በ640 ሚሊየን ዩኤስ ዶላር የሚገነባው እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡ ህንድ በአዲስ አበባ ለሚገኘው የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል 64ሲቲስካን ማሽን በድጋፍ አገልግሎት አበርክታለች፡፡ የፋሽን ቴክኖሎጂ ብሄረዊ ተቋም የማዕከላዊ የሌዘር ምርምር ኢንስቲቲዩት ከኢትዮጵያ የቴክስታይል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቲዩት እና የኢትዮጵያ የሌዘር ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቲዩት ጋር የአቅም ግንባታ ፕሮጀክቶችን ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡

የእርዳታ ፕሮጀክቶች

 1. በርካታ የእርዳታ ፕሮጀክቶች 4 ቢሊየን ዩኤስ ዶላር የሚጠጋ የተለያዩ ዘርፎችን ለምሳሌ መሰረተ ልማት ሀይድሮ ኤሌክትሪክ፣ የሐይል ማስተላለፍ እርሻ፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ኢንዱስትሪ ወዘተ.. በእርዳታ ተቀባይ መንግስታት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሲሆን በአፍጋኒስታን ባንግላዲሽ፣ ቡታን፣ ማይናማር፣ ማልዳይቭስ፣ ኔፓል፣ ስሪላንካ፣ ሞሪሺየስ፣ ሲሼልስ እነ ሌሎች ሀገራት እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ ከህንድ ጎረቤቶች ውጪ በደቡብ ምስራቅ እስያ፣ ማእከላዊ እስያ አፍሪካ እና ላቲን አሜሪካ፣ የሁለትዮሽ ፕሮጀክሮች በኢንፎርሜሽን እና ኮምፒተር ቴክኖሎጂ (አይሲቲ)፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እና የአርኪዮሎጂ ጥበቃ ተከናውኗል፡፡
 2. በህንድ መንግስት የተጠናቀቁ  ፕሮጀክቶች እርዳታ የአፍጋን-ህንድ ወዳጅነት ግድብ በአፍጋኒስታን፣ በካቡን የአፍጋን ፓርላማ ህንፃ ግንባታ፣ በሞሪሺየስ አዲስ የኢኤንቲ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ፣ በሞሪሺየስ የሜትሮ ኤክስፕረስ ፕሮጀክት፣ በሴሪላንካ የጃፍና የባህል ማዕከል፣ በሞሪሺየስ የጠቅላይ ፍ/ቤት ህንፃ ወዘተ… ይገኛሉ፡፡

የአቅም ግንባታ እና የቴክኒክ ድጋፍ

 1. የአቅም ግንባታ ድጋፍ ለህንድ የልማት አጋርነት መርሃ ግብር ጠቃሚ ጉዳይ ነው፡፡ የህንድ መንግስት ለሌሎች ወደጃ ሀገራት በተለያዩ መልኩ ለአቅም ግንባታን ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛልለምሳሌ በህንድ የሲቪል እና ወታደራዊ ስልጠና መርሃ ግብር፣ በውጪ የስልጠና ሳይት፣ የህንድ ባለሙያዎችን በመላክ፣ የልዕቀት ማዕከል በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከላት እና በሙያ ትምህርት ስልጠና ማዕከላት ይገኛሉ፡፡
 2. የህንድ የቴክኒክ እና ልማት ትብብር መርሃ ግብር በ1964 እ.ኤ.አ የተቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በማል አለም በ160 አጋር አገራት ከእስያ፣ አፍሪካ፣ ምስራቅ አውሮፓ፣ ላቲን አሜሪካ፣ ካሪቢያን፣ እንዲሁም ፓስፊክ እና ትናንሽ የደሴት ሀገራት ይሸፍናል፡፡ የህንድ የቴክኒክ እና የኢኮኖሚ ትብብር መርሃ ግብር በአብዛኛው የአጭር ጊዜ ስልጠና ኮርሶችን በየአመቱ በህንድ የመንግስት ተቋማት በተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች፣ ቢሮዎች እና የስራ ባለሙያዎች ያዘጋጃል፡፡ መርሃ ግብሩን በ2006-07 እ.ኤ.አ ከነበረበት 4000 ስልጠናዎች በ2019-20 እ.ኤ.አ ወደ 14000 ስልጠናዎች (የመከላከያ ስልጠናን ጨምሮ) አድጓል፡፡ በ2019-20 እ.ኤ.አ የሲቪል ሰልጣኞች በህንድ የቴክኒክ የኢኮኖሚ ትብብር ከ383 በላይ ኮርሶች በ98 ተቋማት በስፋት ይሰጣል፡፡ ይህም የኢንጂነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ትምህርቶች፣ የመንግስት ስራዎች፣ የአከባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እርሻ፣ ባንክ፣ ፋይናንስ፣ ሂሳብ እና ኦዲት፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ፣ ጤና እና ዮጋ፣ ፔትሮሊየም፣ አይሲቲ፣ ጋዜጠኝነት፣ አስተዳደር እና  አመራር፣ ሀይል፣ ታዳሽ እና አማራጭ ኢነርጂ፣ ሶላርን ጨምሮ፣ የገጠር ልማት፣ ሴቶችን ለስልጣን ማብቃት ወዘተ.. ያካትታል፡፡
 3. አዲስ ትብብሮች ለምሳሌ ኢ-አይቴክ፣ አይቴክ- ኦንሳይት እና አይቴክ ኤክስኪዩቲቭ በህንድ የቴክኒክ እና የኢኮኖሚ ትብብር ከ2018 እ.ኤ.አ ጀምሮ ተካቷል፡፡
 4. በ2019-20 እ.ኤ.አ፣ (i) ከጠቅላላ 400 አይቴክ ስልጠና ውስጥ 369 እና (ii) ከ55 ውስጥ 37 የምረቃ ትምህርት፣ ድህረ ምረቃ እና ፒኤችዲ፣ ለኢትዮጵያዊያን ተሰጥቷል፡፡ በአይኤ ኤፍኤስ III ከኢትዮጵያ ከ2016 እ.ኤ.አ ጀምሮ 166 እኙ ተፈታኞች በተለያዩ የስልጠና መርሃ ግብሮች ለምሳሌ የስራ ክፍፍል የህክምና ስልጠና፣ የከበረ ድንጋይ እና የጌጣጌጥ፣ ፒኤችዲ እና ማስተርስ (እርሻ)፣ የትላልቅ አውራ መንገዶች ምህንድስና፣ ትልቅ ዳታ፣ የንፋስ ኢነርጂ፣ የባህላዊ ህክምና፣ የሶላር ቴክኖሎጂ፣ ፓራሜዲክስ እና ፍሎሪካልቸር ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ኤዩ እና ዩኤንኢሲኤ  በቅደም ተከተል በአይቴክ 15 እና 10 ስልጠናዎችን አግኝተዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ አራት ኢትዮጵያዊያን ከጤና ሚኒስቴር በኢ-አይቴክ መርሃ ግብር በ”በኮቪድ 19 ወረርሽኝ አያያዝ” በዌቢናር ስልጠና ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

 

 

ህንድ ለሰብዓዊነት

 1. በጥቅምት 2018 የ’ህንድ ለሰብዓዊነት’ መርሃ ግብር የማህተመ ጋንዲ 150ኛ የልደት በዓልን ለማክበር እና ለሰው ልጅ ያደረገውን አገልግሎት ታስቦ ተከብሯል፡፡ መንግስታዊ ካልሆነው ባግዋን ማሀቪር ቪክላግ ሳሀያታ ሳሚቲ ድርጅት ጋር በመተባበር በስፋት “ጃይፉር ፉት”  በመባል የሚታወቀውን መርሃ ግብር ለአንድ አመት የቀጠለ የሰው ሰራሽ እግር መግጠሚያ በበርካታ ሀገራት ለማዳረስ ተሞክሯል፡፡ በርካታ የሰውሰራሽ እግር መግጠሚያ ካምፖች በበርካታ የእስያ እና የአፍሪካ ሀገራት ተቋቁመዋል፡፡
 2. ለሁለተኛ ጊዜ ሰው ሰራሽ እግር መግጠሚያ በባግዋን ማሀቪር ቪክላግ ሳሀያታ ሳሚቲ ድርጅት ህዳር/ታህሳስ 2019 እ.ኤ.አ የተቋቋመ ሲሆን በአዲስ አበባ በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከ500 በላይ የአካል ጉዳተኞች የሰው ሰራሽ እግር በነፃ ተገጥሞላቸዋል፡፡ የመጀመሪያው መሰል ካምፕ በባግዋን ማሀቪር ቪክላግ ሳሀያታ ሳሚቲ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ ታህሳስ 2016/ጥር 2017 እ.ኤ.አ በመቀሌ እና ሀሮማያ ዩኒቨርስቲ 650 የሚሆኑ አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
 3. የህንድ ድጋፍ ለኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የአቅም ግንባታ ለጤና ባለሙያዎች በህንድ የቴክኒክ እና ኢኮኖሚ ትብብር እቅድ እና በስኮላርሺፕ/የስልጠና እድሎች (50,000 ለአፍሪካ በህንድ የአፍሪካ ፎረም ሰሚት አማካኝነት) መሳሪያዎች እና መድሃኒቶች ለሆስፒታሎች እንዲሁም ቴሌ-ሜዲሲን አገልግሎት እና ትምህርት በርቀት በኢ-ቪቢኤቢ መርሃ ግብር ተሰጥቷል፡፡ የተከበሩ የህንድ ፕሬዝዳንት ሽሪ ራም ናትኮቪንድ በኢትዮጵያ ጥቅምት 2017 እ.ኤ.አ ባደረጉት ጉብኝት 2 ሚሊየን ዩኤስዲ የሚያወጡ መድሃኒቶች እና 1000 ሜትሪክ ቶን ሩዝ ለኢትዮጵያ መንግስት ሰጥቷል፡፡ 100,000 የትምህርት መጽሀፍት በመጨረሻ ደረጃ ተሰጥቷል፡፡
 4. አሁን ባለው የኮረና ቀውስ ህንድ ከኮቪድ ጋር የተያያዘ የህክምና ድጋፍ የመመርመሪያ መሳሪያ፣ የመሸፈኛ ጭንብሎች፣ እና ሀይድሮክሲ ክሎሮኪን እና ሌሎች መድሃኒቶችን ከ90 በላይ ለሚሆኑ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አለም የፋርማሴቲካል እና መድሃኒቶች አስተማማኝ አቅራቢነቶ በመላው አለም እውቅና የተሰጣት እና የተደነቀችበት ሚና ተጫውታለች፡፡
 5. ከህክምና አገልግሎት አቅርቦት በተጨማሪ ህንድ የቴክኒክ ድጋፍ ፈጣን የምላሽ ሰጪ ቡድን ወደ ኩዌት እና ማልዳይቭስ ልካለች፡፡
 6. በርካታ ኢ-አይቴክ ዌቭ ታዳሚዎች የኮረና ወረርሽኝን ለመከላከል ልምድ በመለዋወጥ ከሌሎች ሀገራት ባለሙያዎች ጋር ምርጥ ተሞክሮዎችን ይለዋወጣል፡፡

 የባህል ትብብር እና የቅርስ ፕሮጀክቶች

 1. በህንድ መንግስት የድጋፍ መርሃ ግብር ከ50 በላይ የባህል እና የቅርስ ፕሮጀክቶች የአናዳ ቤተመቅደስ፣ ሸውዳጎን ፓጎዳ (ማይናማር)፣ የቲሩኬቲስዋራም ቤተመቅደስ እድሳት፣ የሳርናት ቡድሃ ምስል ማቆም፣ የህንድ  ሙዚየም በቅዱስ ቱዝ ሬሊክ ቤተመቅደስ፣ ካንዲ (ስሪላንካ)፣ የተለያዩ ጆንግስ ግንባታዎች፣ ታንጎ የቡድሃ ኮሌጅ (ቡታን)፣ የቫላ ቲሪፑራ ሰንዳሪ ቤተመቅደስ፣ የደራምሻላስ-ፓሹፓቲናት ቤተመቅደስ ግንባታ (ኔፓል)፣ የጊሪሽ ቻንድራ ሴን መኖሪያ ወደ ሙዚየምነት መለወጥ፣ በማልቪቫዛር (ባንግላዲሽ) የማኒፑሪ የባህል ህንፃ፣ የመስጊድ እድሳት (ማልዳይቭስ)፣ የስቶር ቤተመንግስት እድሳት፣ ብሉ መስኪድ (አፍጋኒስታን)፣ ብሄራዊ ቤተመዘክር እና ቤተመጽሀፍት ማቋቋም(ሞሪሺየስ)፣ ብሄራዊ የጦርነት መታሰቢያ መገንባት (በ1ኛው የአለም ጦርነት ለተሰዉ የህንድ ወታደሮች መታሰቢያ) (ፈረንሳይ) የቦሮቡዱር እና የፕራምባናን ቤተመቅደስ (ኢንዶኔዢያ)፣ የጌታ ቡድሃ የስጦታ ሀውልት ለጋንዳን ገዳም (ሞንጎሊያ)፣ ማይ ሰን ግሩፕ ቤተመቅደሶች እድሳት (ቪየትናም)፣ የቫት ፉ ሺቫ ቤተመቅደስ እድሳት (ላኦስ)፣ የታ ፕሮህም፣ አንጎር ዋት፣ ፕሬህ ቪሀር ቤተመቅደሶች እድሳት (ካምቦዲያ)፣ ቶራና በር (ማሌዢያ)ይገኙበታል፡፡ በአሁኑ ሰዓት 25 የሚሆኑ ባህላዊ እና ቅርሳዊ ፕሮጀክቶች በተለያዩ ሀገራት ተግባራዊ በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡

 

 

.
 • Address : 224, Kebele 13/14, Woreda 07, Arada Sub-City, Near Bel Air Hotel, Aware, Addis Ababa, Ethiopia
 • Working : 9:30 am and 11:30 am on all working days, (Mondays to Fridays) except Holidays.
 • Telephone Numbers : 00-251-11-1235538/39/40/41
 • Fax Number : 00-251-11-1235547/1235548
 • E-Mail :hoc.addisababa@mea.gov.in