Amharic rendering of Press Release- Unveiling of the Portrait of former PM Late Atal Bihari Vajpayee

Last Updated on August 17, 2020

የህንድ ምክር ቤት ለባህላዊ ግንኙነት

አዛድ ባቫን፣ ኒው ደልሂ

ጋዜጣዊ መግለጫ

በህንድ ምክር ቤት ለባህላዊ ግንኙነት ዋና መስሪያ ቤት

የሽሪ አታል ቢሀሪ ቫጅሀይ ጂ ምስል   ምረቃ

የህንድ ምክር ቤት ለባህላዊ ግንኙነት በሟች የቀድሞ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር  ሽሪ አታል ቢሀሪ ቫጅሀይ ጂ ምስል በህንድ ምክር ቤት ለባህላዊ ግንኙነት ግቢ ውስጥ ነሐሴ 10 ቀን 2012  የምስል  ምረቃ አድርገዋል፡፡ ስነ ስርአቱ የተዘጋጀው ሽሪ አታል ቢሀሪ ቫጅሀይ ጂ 2ኛ የሙት አመት ማስታወሻ እና ለሀገር ግንባታ ላደረጉት አስተዋጽኦ  ለማሰብ ነው፡፡

የነሀሴ 10 ስነ ሰርአት የተከበሩ የህንድ ፕሬዝዳንት ሽሪ ራም ናት ኮቪንድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሽሪ ቪ.ሙራሊድሀራን እና የህንድ ምክር ቤት ለባህላዊ ግንኙነት ፓላማ አባል ዶ/ር ቪናይ ሳሀስራጉድሄ በተገኙበት የሽሪ አታል ቢሀሪ ቫጅሀይ ጂ የተሳለ ምስል ተመርቋል፡፡ ምስሉ በዘይት ሸራ ላይ በሽሪ ቫሱዶ ካማት የተሰራ ሲሆን ሰሀሊው በሙምባይ የታወቀ ሰሀሊ ሲሆን በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ሜዳሊያዎችን ተሸልሟል፡፡

ሽሪ አታል ቢሀሪ ቫጅሀይ የቀድሞ የህንድ ምክር ቤት ለባህላዊ ግንኙነት ፕሬዝዳንት በመሆን ከመጋቢት 1969 እስከ ነሀሴ 1971 ድረስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆኖ በጃናታ ድህረ አስቸኳይ መንግስት በመሆን አገልግሏል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በነበሩትበት ጊዜ ቪጅፓይ ጂ በ1969 በህንዲ ቋንቋ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉ የመጀመሪያው ሰው ናቸው፡፡ የህንድ ምክር ቤት ለባህላዊ ግንኙነት በተጨማሪ እንዲስፋፋ እና የህንድ በሀል በመላው አለም እንዲታወቅ ራእይ እና መመሪያ የሰጡ ሰው ናቸው፡፡

የፓርላማ አባል፣ የውጭ ጉዳይ ሚስቴር እና በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስቲር  ሽሪ አታል ቢሀሪ ቫጅሀይ በ ህንድ ምክር ቤት ለባህላዊ ግንኙነት ተግባራት ላይ አስደናቂ እና ዘላቂ ተጽእኖ አሳርፈዋል፡፡

የህንድ ምክር ቤት ለባህላዊ ግንኙነት የተቋቋመው ሚያዚያ 1 ቀን 1942  ሲሆን በህንድ የውጭ የበሀል ግንኙነት ፖሊሲዎች መርሀ ግብሮች አተገባበር በንቃት በመሳተፍ የባህል ግንኙነቶችን እና የጋራ መግባባት በህንድ እና በሌሎች ሀገራት መካከል የባህል ልውውጥ ከሌሎች የውጭ ሀገራት እና ህዝቦች ጋር ለማጠናከር ይሰራል፡፡ የህንድ ምክር ቤት ለባህላዊ ግንኙነት 19 የክልል ጽ/ቤቶች በተለያዩ የህንድ ሀገራት እና በመላው አለም  በውጭ 38 የባሀል ማዕከላት በመክፈት ፕሮግራሙን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ላለፉት አመታት የህንድ ምክር ቤት ለባህላዊ ግንኙነት በመጠን እና በተግባር ያደገ ሲሆን በአሁኑ ሰአት የህንድን ሀይል በውጭ ፕሮጀክት ስልጣን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የባህል ዲፕሎማሲ ሀይል በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡


  • Address : 224, Kebele 13/14, Woreda 07, Arada Sub-City, Near Bel Air Hotel, Aware, Addis Ababa, Ethiopia
  • Working : 09:00 am and 11:30 am on all working days, (Mondays to Fridays) except Holidays.
  • Telephone Numbers : 00-251-11-6362010
  • E-Mail :hoc[dot]addisababa[at]mea[dot]gov[dot]in

Visitors Count:

Last Updated on: April 16, 2024 @ 2:02 pm